ወንፈል ተራድዖ
ወንፈል ተራድዖ ርጅት እንደ ኤሮፖዊያን አቆጣጠር በ2018 በሰሜን አሜሪካን ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ የተመሰረተ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው::ወንፈል ተራድዖ “የተሰጠንን እንሰጣለን " በሚል መርህ በተሰባሰቡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በካሊፎርኒያ የ501 c ፈቃድ አግኝቶ የሚንቀሳቀስ : መንግስታዊ ያልሆነና ለትርፍ ያልተቋቋመ ህጋዊ ድርጅት ነው:: ወንፈል ተራድዖ ከምስረታው ማግስት ጀምሮ : የማህበረሰባቸውን ወንፈል ለመክፈል ቁርጠኛ የሆኑ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበርና ከ 6.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ፈሰስ በማድረግ - በትምህርት : - በጤና - በእርሻ ቴክኖሎጅ - በወላጅ አልባ ህፃናት እንክብካቤና - በአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ ዘርፍ በርካታ ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን በተለይም በአማራ ክልል ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ : እየሰራ ይገኛል ::
የአማራ ህዝብ በተደጋጋሚ በሚያጋጥመው ተፈጥሯዊ ና ሰውሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለረጅም ዘመን ለከፋ ድህነትና ጉስቁልና ተጋልጦ የኖረ ህዝብ ነው:: ይህ ህዝብ በተደጋጋሚ ለተለያዩ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች ተጋላጭ እንዲሆን በመደረጉ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን አሁንም እያስተናገደ ይገኛል ::በተለይም ከኦሮሚያና ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ተፈናቅለው የመጡ ዜጎች ቁጥር እጅግ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ: አሁን በተከፈተው ጦርነት ምክንያት የብዙ ሴቶችና ህፃናት ህይወት ለከፋ ጉስቁልና ተጋልጦአል :: በአሁኑ ሰኣት በአማራ ክልል ብቻ 11 ሚሊዩን የሚሆኑ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችም በጦርነቱ ምክንያት አካባቢያቸው በመውደሙ አስቸኳይ የመልሶ ማቋቋም እርዳታ ይሻሉ :: ወንፈል ይህንን ዘርፈ ብዙ ችግር በመጋፈጥ 540 የሚሆኑ ወላጅ አልባ ህፃናትን እስፖንሰር በማድረግና የምግብ : የአልባሳት: የትምህርት ቁሳቁስና: መጠለያ በማቅረብ እያስተማረ ይገኛል ::
ወንፈል በጦርነቱ ምክንያት የተለያየ ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ድጋፍ በማድረግና በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ቁጥራቸው ወደ 600 ለሚሆኑ ህፃናትና ሴቶች በቀን ሁለቴ የመመገብ ፕሮጀክቶች ያሉት ሲሆን ባሎቻቸውን ደግሞ በጦርነቱ ያጡ ቤተሰቦችን ደግሞ በተለየ ሁኔታ ለማገዝ የሚያስችልና ለጋራ የእርሻ ስራ የሚውሉ ትራክተሮችንም ገዝቶ ለማቅረብ ችሏል :: እንግዲህ ከብዙ በጥቂቱ የወንፈል ጥረቶች እነዚህ ሲሆኑ አሁንም ሰፉፊ ፕሮጀክቶችን ለማከናዎን የእርስዎን እርዳታ በእጅጉ ይሻል :: በመሆኑም በወር ከ 25- 30 ዶላር ብቻ በማዋጣት አንድ ወላጅ አልባ ህፃን እስፖንሰር ከማድረግ ጀምሮ በምናዘጋጃቸው እርዳታ የማሰባሰብ ፕሮግራሞች ላይ በንቃት በመሳተፍ ወንፈልዎን እንዲወጡ እየጋበዝን በበለጠ ለመረዳት ደግሞ WWW.WONFEL.ORG ድህረ ገፃችንን በመጎብኘትና አቅምዎ በሚችለው መጠን ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እንጋብዛለን !! ልብ ይበሉ የሚለግሷት እያንዳንዷ ሽርፍራፊ ሳንቲም የብዙዎችን ህይወት ትታደጋለች :: ተሥፋቸውንም ታለመልማለች !!
የተሰጠንን እንሰጣለን ! ወንፈል ተራድዖ